
Retired
This book is no longer available for sale.
Pinocchio ፒኖኪዮ
አባ ዮሴፍ ገና ንግግሩን ከመጨረሱ ያች የምትመጣበት ስፍራ የማይታወቅ ረቂቅ ድምጽ - ጐሽ ጐሽ አባ ሽሮ - እያለች ጮኸች።
አባ ዮሴፍም አባ ሽሮ መባሉን በሰማ ጊዜ እንደ በርበሬ እስኪቀላ ተናዶ ተንጠራርቶ ዓይኑን በአናጢው አፍጥጦ - እቤትህ መጥቼ እንዴት እንደዚህ ትለኛለህ? ብሎ ጮኸበት።
- ምን አልኹ? ምን አጠፋሁ? - አባ ሽሮ አልኸኝ! - አላልሁም! - ታዲያ እኔ ነኝ? አንተ ነህ! - አይደለሁም! - አንተ ነህ! - አይደለሁም! - አንተ ነህ አንተ ነህ!
ነገሩ እየተጋጋለ ሰለሔደ ተናነቁ ተደባደቡ ተሰዳደቡም ከአምባጓሮውም በኋላ አያ ቲማቲሞ አባ ዮሴፍን እንደ ቆብ የደፋው የውሸት ሽበት በእጁ መኖሩን አየ፤ አባ ዮሴፍም የአያ ቲማቲሞን የውሸት ሽበት በጥርሱ እንደነከሰ፤
- አያ ቲማቲሞ ሽበቴን መልስ - እያለ ተነፋነፈ - አንተም የኔን ትፋ! - ብሎ አያ ቲማቲሞ ሽበቱን ከአባ ዮሴፍ ከተቀበለ በኋላ እጅ ለእጅ ተጨባብጠው ህይወታቸውን ሙሉ መልካም ወዳጆች ሁነው እንዲኖሩ ተማማሉ። ሰላምም ከሆነ በኋላ - አናጢው - አባ ዮሴፍ ኧረ ምን ኑሯል የምትፈልገው - አለ። - ምስሉን የምሠራበት ትንሽ እንጨት እፈልግ ነበር። ትሰጠኛለህ?
አያ ቲምቲሞ ደስ ብሎት ያን ዘወትር የሚያስደነግጠውን የእንጨት ቁራጭ ከጠረጴዛ አንስቶ ለሽማግሌው ሊሰጥ ሲቀርብ እንጨቱ ተንፈራግጦ እንደ አሳማ እተድበለበለው አባ ዮሴፍ ጭን ላይ ወደቀ።
- አዬ ያንተ ነገር! ለሰው እቃ ስትሰጥ በእንደዚህ ያለ ትሕትና ነው የምትሰጠው? ሰነከልከኝ እኮ! - እኔ አይደለሁም እምላለሁ! - ታዲያ እኔ ነኝ! - ጥፋቱ ሁሉ የዚህ እንጨት ነው። - ጥፋቱ የእንጨቱ መሆኑን አውቃለሁ ነገር ግን እግሬ ላይ የወረወርኸው አንተ ነህ! - እኔ አልወረወርኩብህም! - ውሸታም! - አባ ዮሴፍ ተው አትስደበኝ! አለዚያ አባ ሽሮ እልሃለው! - አህያ! - አባ ሽሮ! - ውሻ! - አባ ሽሮ! - ቂል ዝንጀሮ! - አባ ሽሮ!
About
About the Book
በኢትዮጵያ ሰዎች ዘንድ የሚያስመስግነኝ ነው በማለት ካርሎ ኮሎዲ የተባለው የኢጣሊያ ጸሐፊ የጻፈውን ፒኖኪዮ ተብሎ የተሰየመውን በዓለም የታወቀውን ስመ ጥሩውን ቆንጆውን የኢጣሊያ መጽሐፍ በአማርኛ ለመተርጎም በሙሉ እምነት ተነሣሁ።
ይህ መጽሐፍ ለወጣቶችና ለሕፃናት ብቻ አልተጻፈም። ታላላቆችም በደስታና በሚያጫውት ንባብ ትንሽ ጊዜያቸውን እንዲያሳልፉ በማለትም እንጂ ነው።
ፒኖኪዮ በውነት በሁሉ ቋንቋ የተተረጎመ በዓለም የተደነቀ ስመ ጥሩ መጽሐፍ በመሆኑ ከብዙም ዘመናት ጀምሮ ለዓለም ሕፃናት ሁሉ ደስታና አጫዋች ሁኖ ይኖራል።
የኢትዮጵያ ወጣቶች ይኽነኑ ዓይነት ደስ የሚያሰኝ ንባብ እያነበቡ እንዲጫወቱና ሲጫወቱ ወዲያውም እንዲማሩ ይኽነን መጽሐፍ ማዘጋጀት የሚገባ መሆኑ ተሰማኝ።
ፒኖኪዮ ይልቁንም ልጆችንም የሚያስተምርና የሚመራ መጽሐፍ ነው። ምንም የሃይማኖት ነገር በፍጹም በውስጡ ባይኖር አእምሮ የሚከፍት መጽሐፍ ነው። ይልቁንም ደግሞ ከእውነት የወጣ ልዩ ታሪክ እያወራ አእዋሳትንም ያለ ባሕርያቸው ባሕርያ እየሰጣቸው ለማሣቅና ለማስደነቅ የተመቸ ውብ መጽሐፍ ሆኖ ታገኙታላችሁ። ብዙም ጊዜ ያስቃል፤ ብዙ ጊዜ ያሳዝናል፤ ብዙ ጊዜ የልጆችን ደካማነት ምን ያህል እንደሆነ ያሳያል፤ በዚህም ስጦታው ነገሩን እየገለበጠ እየዘረዘረና እያሳየ ልጆች ሊያደርጉት የሚገባቸውንና ላያደርጉት የማይገባቸውን ከታላቅ ጥፋትም የሚያደርሰውን ወደ በጎ የሚመራውን ከክፉ ጓደኛ መዋል የሚያመጣውን ችግርና ሁኔታ ሁሉ እየለየ በሰፊው ያሳያቸዋል።
ፒኖኪዮ በአማርኛ ወልደ እንጨት ብዬ የተረጎምኩት እንደ ሰው የሚላወስ የሚናገር የሚስቅ የሚያለቅስ ይልቁንም የልጆች ጠባይ ያለው አንድ የእንጨት ምስል ነው። ከብዙ ብዙ ድካምና ታሪክም በኋላ በመጨረሻው ወልደ እንጨት እንደ ሰው ልጅ አጽምና ሥጋ ለብሶ በዚህ ሁሉ ላይ ደህና ሰውነትና የሥራ ወዳድነት ባሕርይ ያደረበት በውኑ ፍጹም ሰው ይሆናል።
ይኽን አከናውኜ ያቀረብኩላችሁን ስመ ጥሩ መጽሐፍ ምንም ሃይማኖት ሳይቃወም እንደ ጨዋታ እያደረገ የሚያስተምር ሙሉ የምክር ቃልና ደስ የሚያሰኝ አእምሮ የሚያነቃ የንባብ መጽሐፍ ስለሆነ አንባቢው ሳይታወቀው ያለ ማቋረጥ እየተማረና እየተመከረ ንባቡን ይከተላል። ይኸውም መጽሐፍ ፍሬ ነገሩን ለተረዳው ሰው መጽሐፍ መሆኑ ቀርቶ የፈቃደኛና የትጉህ መልካምነት ምክር ይመስላል።
ከኔ ጋራ ሁኖ ብዙውን ሥራ ያከናወነልኝን አቶ ጥላሁን ቸርነትን በብዙ አመሰግናለሁ። ደግሞም ጽሕፈቴን አንብበው ከመጽሐፉም መታትም በፊት ቃሉን ያሻሻሉልኝን ምክር የሰጡኝንና ሁሉ አመሰግናለሁ።
Author
About the Author
Causes
Causes Supported

The Leanpub 60 Day 100% Happiness Guarantee
Within 60 days of purchase you can get a 100% refund on any Leanpub purchase, in two clicks.
Now, this is technically risky for us, since you'll have the book or course files either way. But we're so confident in our products and services, and in our authors and readers, that we're happy to offer a full money back guarantee for everything we sell.
You can only find out how good something is by trying it, and because of our 100% money back guarantee there's literally no risk to do so!
So, there's no reason not to click the Add to Cart button, is there?
See full terms...
Earn $8 on a $10 Purchase, and $16 on a $20 Purchase
We pay 80% royalties on purchases of $7.99 or more, and 80% royalties minus a 50 cent flat fee on purchases between $0.99 and $7.98. You earn $8 on a $10 sale, and $16 on a $20 sale. So, if we sell 5000 non-refunded copies of your book for $20, you'll earn $80,000.
(Yes, some authors have already earned much more than that on Leanpub.)
In fact, authors have earned over $14 million writing, publishing and selling on Leanpub.
Learn more about writing on Leanpub
Free Updates. DRM Free.
If you buy a Leanpub book, you get free updates for as long as the author updates the book! Many authors use Leanpub to publish their books in-progress, while they are writing them. All readers get free updates, regardless of when they bought the book or how much they paid (including free).
Most Leanpub books are available in PDF (for computers) and EPUB (for phones, tablets and Kindle). The formats that a book includes are shown at the top right corner of this page.
Finally, Leanpub books don't have any DRM copy-protection nonsense, so you can easily read them on any supported device.
Learn more about Leanpub's ebook formats and where to read them
Write and Publish on Leanpub
You can use Leanpub to easily write, publish and sell in-progress and completed ebooks and online courses!
Leanpub is a powerful platform for serious authors, combining a simple, elegant writing and publishing workflow with a store focused on selling in-progress ebooks.
Leanpub is a magical typewriter for authors: just write in plain text, and to publish your ebook, just click a button. (Or, if you are producing your ebook your own way, you can even upload your own PDF and/or EPUB files and then publish with one click!) It really is that easy.