Email the Author
You can use this page to email ኢትዮጵያ about Pinocchio ፒኖኪዮ.
About the Book
በኢትዮጵያ ሰዎች ዘንድ የሚያስመስግነኝ ነው በማለት ካርሎ ኮሎዲ የተባለው የኢጣሊያ ጸሐፊ የጻፈውን ፒኖኪዮ ተብሎ የተሰየመውን በዓለም የታወቀውን ስመ ጥሩውን ቆንጆውን የኢጣሊያ መጽሐፍ በአማርኛ ለመተርጎም በሙሉ እምነት ተነሣሁ።
ይህ መጽሐፍ ለወጣቶችና ለሕፃናት ብቻ አልተጻፈም። ታላላቆችም በደስታና በሚያጫውት ንባብ ትንሽ ጊዜያቸውን እንዲያሳልፉ በማለትም እንጂ ነው።
ፒኖኪዮ በውነት በሁሉ ቋንቋ የተተረጎመ በዓለም የተደነቀ ስመ ጥሩ መጽሐፍ በመሆኑ ከብዙም ዘመናት ጀምሮ ለዓለም ሕፃናት ሁሉ ደስታና አጫዋች ሁኖ ይኖራል።
የኢትዮጵያ ወጣቶች ይኽነኑ ዓይነት ደስ የሚያሰኝ ንባብ እያነበቡ እንዲጫወቱና ሲጫወቱ ወዲያውም እንዲማሩ ይኽነን መጽሐፍ ማዘጋጀት የሚገባ መሆኑ ተሰማኝ።
ፒኖኪዮ ይልቁንም ልጆችንም የሚያስተምርና የሚመራ መጽሐፍ ነው። ምንም የሃይማኖት ነገር በፍጹም በውስጡ ባይኖር አእምሮ የሚከፍት መጽሐፍ ነው። ይልቁንም ደግሞ ከእውነት የወጣ ልዩ ታሪክ እያወራ አእዋሳትንም ያለ ባሕርያቸው ባሕርያ እየሰጣቸው ለማሣቅና ለማስደነቅ የተመቸ ውብ መጽሐፍ ሆኖ ታገኙታላችሁ። ብዙም ጊዜ ያስቃል፤ ብዙ ጊዜ ያሳዝናል፤ ብዙ ጊዜ የልጆችን ደካማነት ምን ያህል እንደሆነ ያሳያል፤ በዚህም ስጦታው ነገሩን እየገለበጠ እየዘረዘረና እያሳየ ልጆች ሊያደርጉት የሚገባቸውንና ላያደርጉት የማይገባቸውን ከታላቅ ጥፋትም የሚያደርሰውን ወደ በጎ የሚመራውን ከክፉ ጓደኛ መዋል የሚያመጣውን ችግርና ሁኔታ ሁሉ እየለየ በሰፊው ያሳያቸዋል።
ፒኖኪዮ በአማርኛ ወልደ እንጨት ብዬ የተረጎምኩት እንደ ሰው የሚላወስ የሚናገር የሚስቅ የሚያለቅስ ይልቁንም የልጆች ጠባይ ያለው አንድ የእንጨት ምስል ነው። ከብዙ ብዙ ድካምና ታሪክም በኋላ በመጨረሻው ወልደ እንጨት እንደ ሰው ልጅ አጽምና ሥጋ ለብሶ በዚህ ሁሉ ላይ ደህና ሰውነትና የሥራ ወዳድነት ባሕርይ ያደረበት በውኑ ፍጹም ሰው ይሆናል።
ይኽን አከናውኜ ያቀረብኩላችሁን ስመ ጥሩ መጽሐፍ ምንም ሃይማኖት ሳይቃወም እንደ ጨዋታ እያደረገ የሚያስተምር ሙሉ የምክር ቃልና ደስ የሚያሰኝ አእምሮ የሚያነቃ የንባብ መጽሐፍ ስለሆነ አንባቢው ሳይታወቀው ያለ ማቋረጥ እየተማረና እየተመከረ ንባቡን ይከተላል። ይኸውም መጽሐፍ ፍሬ ነገሩን ለተረዳው ሰው መጽሐፍ መሆኑ ቀርቶ የፈቃደኛና የትጉህ መልካምነት ምክር ይመስላል።
ከኔ ጋራ ሁኖ ብዙውን ሥራ ያከናወነልኝን አቶ ጥላሁን ቸርነትን በብዙ አመሰግናለሁ። ደግሞም ጽሕፈቴን አንብበው ከመጽሐፉም መታትም በፊት ቃሉን ያሻሻሉልኝን ምክር የሰጡኝንና ሁሉ አመሰግናለሁ።
About the Author